መግቢያ
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ሰማዕት ዘእንበለ ደም አለቃ አያሌው ታምሩ ከ፲፱፻፹ወ፰ (1988) ዓመተ ምሕረት እስከ ፲፱፻፺ወ፱ (1999) ዓመተ ምሕረት ድረስ በመኖሪያ ቤታቸው እየተገኙ ለሚማሩ ተማሪ ዎቻቸው በእየሳምንቱ ቅዳሜ የሚያስተምሯቸውን ትምህርታተ ቃለ እግዚአብሔር በእየጊዜው በራሱ መቅርፀ ድምፅ (ቴፕሪከርደር) እየቀረፀ ያሰባስብ የነበረው ከብላቴንነቱ ጀምሮ ደቀ መዝሙራቸው የኾነው ሣሙኤል ኃይሉ በኹለት ሺኅ ዓመተ ምሕረት እንድማርባቸውና መንፈሳዊ ዕውቀት እንዳገኝባቸው ሰጥቶኝ ስማርባቸው ቆይቻለሁ ፡፡
የሀገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛ ሀብቶች የኾኑ ስለቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት ሥርዓትም ስለሃይማኖትና ባህል ዘመን አቈጣጠ ርና ሰንደቅ ዓላማ ታሪክና ቋንቋ ስለፊደልና ትውፊት ስለሥርዐተ አስተዳደርና ስለመሳሳሉት ጉዳዮች የተላለፉ የሊቁ መምህራችን አለቃ አያሌው ታምሩ ትምህርቶች ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በነፃ እንዲ ዳረስ በማሰብ በ www.Danielgebremeskel.com ድህረ ገጽ የለቀቅኹት (የሚገኝ) ሲኾን አርእስቱም የሚከተሉት ናቸው ፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልኘ
እግዚአብሔር ይባርክህ! ታላቅ ሥራ ነው። ለማመስገን ቃላት የለኝም።